ማዕድን በቦኖ - ቦኖጲያ
የድንጋይ ካባ ስራ መሬት ከመንግስት በመከራየት ይጀምራል። የቁፋሮ ስራ በሰው ሀይል ወይም በማሽን የታገዘ ሊሆን ይችላል። በካባ ውስጥ ሁለት ዋና ዋና የስራ አይነቶች አሉ። እነሱም የድንጋይ ፈላጮች እና የገረጋንቲ ኮረት ሰብሳቢዎች ስራዎች ናቸው። በአብዛኛው ሴቶች በቀን ስራ በባሬላ ኮረት በመሰብሰብ ስራ ላይ ይሰማራሉ። የተወሰኑ ሴቶች ለሰራተኞች ምግብ እና ሻይ ቡና በማቅረብም ይሰማራሉ።
የቀን ሰራተኞች በመጀመሪያ በዶማና አካፋ ከላይ የሚገኘውን አፈር ያነሳሉ። በመቀጠል ፈላጮች በመራጃ ዲጅኖ በመሳሰሉት መሳሪያዎች በመታገዝ ከላይ ወደ ታቻ ድንጋዩን ፈልፍሎ በማውጣት እና መሬቱ ቀጥ ብሎ የቆመ ግንብ የሚመስል ግፅታ እንዲኖረው በማድረግ ፣ የነጭ ወይም የጥቁር ድንጋይ ምርት ያወጣሉ። ምርቱም በገባልጭ መኪና በጫኚዎች አማካኝነት በሜትር ኩዩብ እየተለካ ይጫናል። በተጫነው ጭነት መጠን መሰረት የፈላጩ ድርሻ በተቆጣጣሪ ካቦ አማካኝነት ሂሳቡ ተሰልቶና ተመዝግቦ ለጭነቱ እንደማረገጋጫ ቦኖ ወይም ትኬት ይሰጣል።
የማዕድን መግዣ ማረጋገጫ ደረሰኝም በሶስት ኮፒ ተዘጋጅቶ የመጀመሪያው ለደንበኛው ይሰጣል። ሁለተኛው ለማዕድን ቢሮ፣ ሶስተኛው ለሂሳብ ክፍል አራተኛው ከፓዱ ጋር ቀሪ ይሆናል።
ቅዳሜ ቅዳሜ ለሙስሊሙ ለብቻ ለክርስቲያኑ ለብቻ በግ ታርዶና ተጠብሶ ቡና እየተፈላና ጠጅና ጠላ እየተጠጣ ፈላጮችን ጨምሮ ለሰራተኞች በሙሉ ቦኖውን ከባንክ በወጣ ዝርዝር ብር አማካኝነት ልውውጥ በማድረግ የደሞዝ ክፍያ ይከናወናል። በዱቤ ምግብ ሲያዘጋጁ የነበሩት ሴቶችም ሂሳባቸው ከሰራቶኞቹ ያወራርዳሉ።
የዚህ አይነት የቦኖ የሂሳብ አያያዝ አሰራር በስጋ ቤቶችም በብዛት ይታያል። አዲሱ የክታበ መዛግብት ቴክኖሎጂ እንደዚህ የእለት ተለት የልውውጥ እና ግብይት ስርአት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ምን ይሆናል?
አፈር ስሆን እንብላ በሞቴ
የተባረከ ይሁን
የቄሳርን ለቄሳር!
ዲጂታል ኢትዮጵያ